አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመምረጥ ከ130 በላይ ካርዲናሎች በቫቲካን ተሰብስበዋል

You are currently viewing አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመምረጥ ከ130 በላይ ካርዲናሎች በቫቲካን ተሰብስበዋል

AMN – ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም

“በቁልፍ የተቆለፈ” የሚል ትርጉምን ከሚሰጠው የላቲን “cum clave” ከሚል ቃል የመጣው conclave (የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት) ምርጫ በዝግ የሚደረግ መሆኑን ተከትሎ የተሰጠው ስያሜ ነው።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን እረፍት ተከትሎ ይህ አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን በዝግ የመምረጥ ስነ-ስርዓትን ለማስጀመር ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ከ130 በላይ ካርዲናሎች በቫቲካን ተሰብስበዋል።

ዛሬ ከሰአት በኋላ ካርዲናሎች ድምፃቸውን ለመስጠት ወደ ሲስቲን ቻፕል የሚሄዱ ሲሆን የሞባይል ስልክ ሲግናል በቫቲካን መቋረጡን ተከትሎ ወደ ጸሎት ቤቱ ከገቡ አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እስኪመረጡ ድረስ ከውጪው ዓለም ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አይኖራቸውም።

ከመጀመሪያው ድምጽ አሰጣጥ በኋላ ከሲስቲን ቻፕል ጭስ ማውጫ ጭስ የሚወጣ ሲሆን የጭሱ ቀለም የምርጫውን ሂደት የሚያመላክት ነው። ጥቁር ጭስ ማለት ነገ ተጨማሪ ምርጫ ይካሄዳል ማለት ሲሆን ነጭ ደግሞ አዲስ ጳጳስ መመረጡን የሚያመላክት ነው ።

ይህ ሂደት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ የማይታወቅ ሲሆን ምንም እንኳን ቀደም ባሉት ምዕተ-አመታት ባለመግባባቶች ምክንያት ለወራት የተራዘሙ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫዎች ታይተው ቢታወቁም የቅርቦቹ ግን ለጥቂት ቀናት ብቻ የቆዩ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review