አዲስ አበባን ሳቢና ለኑሮ ምቹ አድርገን ለትውልድ እናሻግራለን ሲሉ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ

You are currently viewing አዲስ አበባን ሳቢና ለኑሮ ምቹ አድርገን ለትውልድ እናሻግራለን ሲሉ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ

AMN- ሰኔ 16/2017

ከአባቶች የተረከብናትን አዲስ አበባን ሳቢና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን አድርገን ለትውልድ እናሻግራለን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።

አቶ ሞገስ ትላንት ምሽት በየካ ክፍለ ከተማ ህብረተሰቡ በራስ ተነሳሽነት ያለማቸውን መንደሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

መንግስት አዲስ አበባን ምቹ ለማድረግ የመንገድ ተደራሽነትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን በስፋት እየሠራ ይገኛል ያሉት አቶ ሞገስ ከዚሁ ጋር በተጣጣመ መልኩ የመኖሪያ ሰፈሮችን ደረጃ በማሻሻል ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ማስቻሉ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

አካባቢው ከዚህ ቀደም ጨለማና በተለይም በክረምት ወቅት ወጥቶ ለመግባት አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ ከህጻናት እስከ አዛውንቶች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት መሆን መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ በራሱ ተነሳሽነት የሰራውን ይህን በጎ ስራ መጠበቅና መንከባከብ ይገባልም ብለዋል።

በቀበና አካባቢ የተከናወነው የሰፈር ልማት ስራ ለሌሎችም ተምሳሌት መሆኑን ገልጸው አሁንም አመራሩ ከህብረተሰቡ ጋር ተባብሮ ስራዉን በሁሉም ብሎኮችና አካባቢዎች ማስፋት ይገባል ብለዋል።

አቶ ሞገስ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባውን ባለ 2ወለል ህንጻ ፖሊስ ጣቢያንም የጎበኙ ሲሆን ሰላሟ የተጠበቀና የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች ከተማን ለቀጣይ ትውልድ እናስረክባለን ብለዋል።

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review