አዲስ አበባ በከተማ ግብርና ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ

You are currently viewing አዲስ አበባ በከተማ ግብርና ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ

AMN – ሰኔ 14/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማን በከተማ ግብርና ዘርፍ ከአፍሪካ ከተሞች ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሼቦ ተናግረዋል ።

መንግስት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋትን ባለፉት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች በዜጎች ህይወት እና የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ረገድ ለውጥ መመዝገቡን ኮምሸነሩ ገልፀዋል ።

በተለይም ጥራት ያለውና በቂ ምርት ለማቅረብ በእርባታ ዘርፉ የመኖ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ኮሚሽኑ በማህበራት የተደራጁ ከመኖ አምራቾች ጋር በመነጋገር በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል ።

ኮሚሽኑ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ከሚሆኑ አርሶአደሮችና አርብቶ አደሮች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በአይናለም አባይነህ እና በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review