
AMN ግንቦት 07/2017
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባስተላለፉት መልእክት አዲስ አበባ ባለ አዲስ ራእይ ከተማ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ከተማ የሰው ልጅ ሥልጣኔ ማሳያ ነው። የአንድ ሀገር ሥልጣኔ የሚለካው በከተሞቿ ደረጃ ነው። ከተማ ሰው ሠራሽ የሰው ልጅ የሥልጣኔ ማዕከል በመሆኑ የኢትዮጵያን የብልጽግና ሞዴል ምን እንደሚመስል ማየት የፈለገ እየተገነቡ ያሉትን ከተሞቻችንን ይመልከት። አዲስ አበባ ባለ አዲስ ራእይ ሆናለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡
