አዲስ አበባ ከተማ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክራ እንደምትቀጥል አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ

You are currently viewing አዲስ አበባ ከተማ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክራ እንደምትቀጥል አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ

AMN – ሰኔ 05/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ ያሉባትን ችግሮች በመልካም ልምዶቿ በመቀየር የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ አጠናክራ እንደምትቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ፡፡

“መልካም ልምዶችንና ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ የጠንካራ ፖርቲ ግንባታ እውን እናደርጋለን” በሚል መሪ ሀሳብ የብልጽግና ፓርቲን የስኬት ጉዞ የሚያሳይ ከተማ አቀፍ የፎቶ አውደ-ርዕይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፈለ ከተማ ለእይታ ክፍት ሆኗል፡፡

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻን ጨምሮ የፓርቲው ከፈተኛ አመራሮች፣ ደጋፊዎች እና የክፍለ ከተማ አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል፡፡

የፎቶ አውደ-ርዕዩን መርቀው የከፈቱቱ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ ፓርቲዉ ባለፉት ዓመታት ያሳለፋቸዉን የስኬት ጉዞ በምል ማስቀረቱ ለነገ ትምህርት የሚሆን ነዉ ብለዋል፡፡

በዚህም ከተማዋ የነበሩባትን ችግሮች ወደ እድል በመቀየር የለዉጥ ጉዞዋን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

በሚቀጥሉት ወራትም ከተማዋ የወጠነቻቸዉ የልማት ንቅናቄዎች ላይ በንቃት መሳተፍ ከሁሉም የሚጠበቅ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በፎቶ አዉደ- ርዕዩ የ11ም ክፍለ ከተሞች የብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ፅሕፈት ቤት አደረጃጃት ዘርፎች ተሳትፈዋል፡፡

በሩዝሊን መሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review