አዲስ አበባ የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማኅበር ዋና መቀመጫ ሆና ተመረጠች

You are currently viewing አዲስ አበባ የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማኅበር ዋና መቀመጫ ሆና ተመረጠች

AMN – ሚያዝያ 01/2017

በቱርክ ኢስታንቡል እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የሎጂስቲክስ ማኅበራት ጉባኤ፥ አዲስ አበባ ከተማን የማኅበሩ ዋና መቀመጫ አድርጎ መምረጡ ተገለጸ።

ይህን የገለጹት ኢትዮጵያን ወክለው በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የኢትዮጵያ የዕቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማኅበር አቶ ዳዊት ውብሸት ናቸው።

በቱርክ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባኤ ላይ 35 ሀገራት ተሳታፊ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዳዊት ውብሸት፥ ኢትዮጵያ የቦርድ ወንበር ማግኘቷንም ይፋ አድርገዋል።

የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ይህን ያስታወቁት የሎጂስቲክስ እና ትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ እየተከናወነ በሚገኝበት መድረክ ላይ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን የዓለም የእቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር (ፊያታ) ጠቅላላ ጉባኤን በመዲናዋ አዲስ አበባ እንደምታስተናግድም ተገልጿል።

በበላይሁን ፍስሃ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review