አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ የሚያሳይ ነው:- የመከላከያ ሰራዊት አባላት

You are currently viewing አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ የሚያሳይ ነው:- የመከላከያ ሰራዊት አባላት

AMN – የካቲት 26/2017 ዓ.ም

ባለፈው ቅዳሜ የተመረቀው የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በበርካቶች እየተጎበኘ ይገኛል።

በዛሬው እለትም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየጎበኙት ነው፡፡

የሀይማኖት አባቶች፣አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማዕከሉን ከጎበኙት መካከል ናቸው።

የኢትዮጵያ ከፍታ ማሳያ እንዲሁም የተሻለ የኢኮኖሚ ምንጭ ይሆናል ተብሎ የታመነበት ማዕከሉ፣ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችንና አገልግሎቶችን አካቶ ነው ለአገልግሎት የበቃው።

ማዕከሉ የተሰራበት እሳቤ፣ ያካተታቸው መሰረተ ልማቶችና ሀገራዊ ፍይዳው የጎላ ፕሮጀክት መሆኑን ተመልክተናል ያሉት ጎብኚዎቹ የተሰሩ ስራዎችን አድንቀዋል።

ሀገር በከፍታ ጉዞ ላይ መሆኗን የሚያሳይ ማዕከል መሆኑንም ተመልክተናል ያሉት ጎብኝዎቹ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ተደማሪ ድምቀትና የገቢ ምንጭ መሆኑንም ነው የጠቆሙት።

በፈቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review