አዳዲስ የትራፊክ ቁጥጥር አሰራሮች በመዘርጋታቸው የትራፊክ አደጋ እየቀነሰ መምጣቱ ተገለፀ

You are currently viewing አዳዲስ የትራፊክ ቁጥጥር አሰራሮች በመዘርጋታቸው የትራፊክ አደጋ እየቀነሰ መምጣቱ ተገለፀ

AMN – ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል በትራፊክ ቁጥጥር አዳዲስ አሠራሮች ተግባራዊ በመደረጋቸው የትራፊክ አደጋ ስጋት እየቀነሰ መምጣቱ ተገልጿል፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አበበ ለገሰ እንደገለጹት፣ በከፍተኛ ደረጃ አደጋ የሚከሰትባቸውን አካባቢዎች በመለየት፣ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን መፍታት መቻሉ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ረድቶናል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር በላቸው ተኬ በበኩላቸው፣ በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ ህብረተሰቡን እና ባለድርሻ አከላትን ያሳተፈ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።

በክልሉ ከ2010 ዓ.ም እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በተደረገ ጥናት መሰረት የትራፊክ አደጋ መንስኤ 81 በመቶው በአሽከርካሪዎች ችግር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በትራፊክ አደጋ ዙሪያ በኦሮምኛ ቋንቋ የተሰራ የግንዛቤ ማስጨበጫ መዝሙርም መመረቁን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review