አጀንዳ 2063 እና የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለፀ

You are currently viewing አጀንዳ 2063 እና የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ማስወገድ እንደሚገባ ተገለፀ

AMN – የካቲት 3/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ማስወገድ እንደሚገባ ተገልጿል።

የሴቶች እና ልጃገረዶችን አቅም ለማጎልበት እየሰራ የሚገኘው ጾታ አጀንዳዬ ነው ዘመቻ /GIMAC/ አመራሮች በህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሴቶች እና ልጃገረዶች ዙሪያ መተላለፍ አለባቸው ባሏቸው ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ሁሉ ማስወገድ ይገባል ብለዋል።

መግለጫውን የሰጡት የዘመቻው ዋና ጸሀፊ ዶክተር ሄለን ኬዚዎሀ እ.ኤ.አ. በየካቲት 2023 የአፍሪካ ህብረት አመራሮች እና መንግስታት አንድ ወሳኝ ውሳኔ ማጽደቃቸውን አስታውሰዋል።

ይህም በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ለማስቆም የተደረገ ስምምነት መሆኑን ገልጸው፤ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሪዎቹ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን አንስተዋል።

የኢኮኖሚ መብት ማጣት፣ ደካማ የሕግ ማዕቀፎች፣ እና ጎጂ ባሕላዊ ልማዶች እንደምክንያት ከሚጠቀሱ መካከል መሆናቸውን አመላክተዋል።

የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ሁሉ ማስወገድ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በቅርቡ የሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ ስምምነቱን እንዲያጸድቀው ጠይቀው፤ ግልጽ ሊለካ የሚችል ብሄራዊ የድርጊት መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀት እና የተጎጂ-ማዕከል የምርመራ ሂደትን ማሳደግ እንደሚገባም አመላክተዋል።

በዚህ ድርጊት የተሳተፉ ወንጀለኞችን ለመመርመር እና ለፍርድ ለማቅረብ ገለልተኛ የተጠያቂነት ዘዴዎችን መመስረት እንዳለባቸው መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review