አፍሪካውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሰላም እና አንድነት በጋራ መስራት አለባቸው – ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

You are currently viewing አፍሪካውያን ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሰላም እና አንድነት በጋራ መስራት አለባቸው – ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

AMN-የካቲት 5/2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ሕብረት አባል አገራት ለአፍሪካ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነት ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለፁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ለ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ተሳታፊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የእራት ግብዣ አድርገዋል።

ዋና የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ባደረጉት ንግግር፤ እየተለወጠ ያለውን የዓለም የጂኦ ፖለቲካ እና ጂኦ ኢኮኖሚ በማጤን የሕብረቱ አባል አገራት ለአፍሪካ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነት ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ታየ ኢትዮጵያ ሰላም፣ መረጋጋት እና ራሷን የቻለች አፍሪካ እውን ለማድረግ የታለመው ርዕይ እንዲሳካ የምታደርገውን እንቅስቃሴ በቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በበኩላቸው አፍሪካ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እያጋጠሙ ያሉ ዘርፈ ብዙ ፈተናዎችን ለመሻገር የባለብዙወገን ግንኙነት አስፈላጊነት ትኩረት ሰጥተው ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ተሳታፊዎች በፓን አፍሪካ ዕሳቤ የአፍሪካን ችግር በአፍሪካዊያን የመፍታት መርሆን በመከተል ተቋማዊ አቅምን ማጎልበት እና የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

በእራት ግብዣው ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት እና በርካታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ታድመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review