ኢሎን መስክ ከትራምፕ አስተዳደር ራሱን ማግለሉን አስታወቀ

You are currently viewing ኢሎን መስክ ከትራምፕ አስተዳደር ራሱን ማግለሉን አስታወቀ

AMN – ግንቦት 21/2017 ዓ.ም

ኢሎን መስክ 260 ሺህ ገደማ የሚቆጠሩ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች የተባረሩበት የዶጅ ንቅናቄ ኃላፊ የነበረ ሲሆን ከትራምፕ አስተዳደር መልቀቁን አስታውቋል።

መስክ ትራምፕ ሥልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ ዶጅ እየተባለ የሚጠራው የአሜሪካ የብክንት ቅነሳ መሥሪያ ቤትን በመምራት “ልዩ የመንግሥት ሠራተኛ” ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል።

ሗይት ሐውስ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ኢሎን መስክ በዓመት 130 ቀናትን እንዲሰራ ተሰጥቶት ከነበረው ሃላፊነቱ እንዲነሳ ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ዶጅን እየመራ እንደማይቆይ እና ኃላፊነቱ ጊዜያዊ እንደሆነ ሲያስታውቅ የቆየው ቱጃሩ ሰው ኢሎን መስክ በኤክስ የማኅበራዊ የትስስር ገፁ በኩል በለቀቀው መግለጫ “ፕሬዝደንት ትራምፕ ብክነትን እንድቀንስ ዕድሉን ስለሰጡኝ አመሰግናለሁ፤ ነገር ግን ዶጅ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብሏል።

በትራምፕ የበጀት ረቂቅ አዋጅ እንደተከፋ ባስታወቀ ማግስት ኃላፊነቱን መልቀቁን ይፋ ያደረገው ኢሎን መስክ በትሪሊየን ዶላሮች የሚቆጠር የግብር እፎይታ እና የመከላከያ በጀት እንዲጨምር ያበረታታል የተባለለትን አዋጁን የፌዴራል መንግሥቱን ዕዳ ውስጥ የሚከት ነው ሲል ነቅፏል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ዶጅ ሲሰራ የነበረውን ሥራ የሚያወርድ ነው ሲልም መስክ ተደምጧል።

ኢሎን መስክ የትራምፕ አስተዳደርን ሲቀላቀል 2 ትሪሊየን ዶላር ብክነት እቀንሳለሁ ብሎ የተነሳ ቢሆንም ይህን ቁጥር ወደ 150 ቢሊዮን ዝቅ ማድረጉ ተዘግቧል።

ባለፈው ሚያዚያ ከመንግሥት ኃላፊነት ገሸሽ ብሎ ትኩረቱን የግል ኩባንያዎቹ ላይ እንደሚያደርግ አስታውቆ የነበረው ኢሎን መስክ የሗይት ሐውስ ልዩ ሠራተኛ በነበረበት ወቅት የቴስላ መኪና ሽያጭ 13 በመቶ ማሽቆልቆሉንና የቴስላ የአክሲዮን ገበያም 45 በመቶ ወርዶ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።

በሊያት ካሳሁን

May be an image of 1 person, the Oval Office and text

All reactions:

55Mehretu Fekade and 54 others

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review