AMN – ህዳር 2/2017 ዓ.ም
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና የትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሞሐመድ ሳሌም ኦድ መርዛውግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በሩሲያ ሶቺ ከተማ እየተካሄደ ካለው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን ከሞሪታኒያ አቻቸው ጋር የተለያዩ አህጉራዊ የጋራ ጉዳዮችን ያካተተ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።