ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሠላም እና መረጋጋት የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሠላም እና መረጋጋት የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለጸ

AMN ግንቦት 28 ቀን 2017

በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ያተኮረዉና የኢጋድ አባል ሀገራትን፣ የዓለምአቀፍ ማህበረሰብ አባላትን እንዲሁም ክልላዊ እና ዓለምአቀፍ ድርጅቶችን ያሳተፈ የምክክር መድረክ በጁባ ተካሄዷል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑክም በኢጋድ አዘጋጅነት ከግንቦት 26 – 27 ቀን 2017 ዓ.ም በጁባ በተካሄደው በዚህ የምክክር መድረክ ላይ ተሳትፏል፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያን ልዑክ በመምራት የተሳተፉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ ኢትዮጵያ እንደ ጎረቤት ሀገር ለደቡብ ሱዳን ሠላም እና መረጋጋት የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሠላም በማስፈን ሒደት ለ2018ቱ የሠላም ስምምነት ሙሉ ተግባራዊነት በኢጋድ መር ሂደቶች የምታደርገውን በመርህ ላይ የተመሰረተ ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

አምባሳደር ዘሪሁን የምክክር መድረኩ ሉዓላዊነትን ያገናዘበ፣ ተግባራዊነትን እና ተጨባጭነት፣ መሰረት ያደረገ እና ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ያማተሩ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን በመግለፅ በዚህ ረገድ የቀጠናዊ ድርጅቱ (ኢጋድ) አባል ሀገራት አንድነት ለመፍትሄው ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አፅንኦት መስጠታቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review