“ሀገሬን እገነባለሁ ሀላፊነቴንም እወጣለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ የወጣቶች የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ኬይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)፣ መንግስት እያከናወናቸው ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎች ወጣቱን ማዕከል ያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ዘላቂ ሰላምና እድገት እንዲረጋገጥ ወጣቱ እምቅ አቅሙን እንዲጠቀምም አሳስበዋል።
የሁላችን የሆነችው ኢትዮጵያ በሁላችን መሠራት አለባት ሲሉም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
የውይይት መድረኩ ዓላማም ወጣቶች በሀገረ መንግስትና በሰላም እሴት ግንባታ ዙርያ የሚጠበቅባቸውን ተግባር እንዲያበረክቱ ሀላፊነታቸውንም እንዲወጡ የጋራ አረዳድና ግንዛቤን መፍጠር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በፀጋ ታደለ