ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ አመታት ያደረገችው የግብርናው ዘርፍ ማሻሻያ ከተረጅነት የሚያላቅቅ ውጤቶችን እንድታስመዘገብ አስችሏል- የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች

You are currently viewing ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ አመታት ያደረገችው የግብርናው ዘርፍ ማሻሻያ ከተረጅነት የሚያላቅቅ ውጤቶችን እንድታስመዘገብ አስችሏል- የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች

AMN- ጥር 21/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ አመታት ያደረገችው የግብርናው ዘርፍ ማሻሻያ የምግብ ዋስትናዋን የሚያረጋግጥና ከተረጅነት የሚያላቅቅ ውጤቶችን እንድታስመዘገብ ማስቻሉን የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተናገሩ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ሀገር የመምራት እድሉን ካገኘ ጀምሮ የኢኮኖሚ ስብራቶችን የሚጠግኑ የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ካደረገባቸው ዘርፎች መካከል የግብርናው ዘርፍ አንዱና ዋነኛው ተደርጓል፡፡

የተለያዩ ተነሳሽነቶችም ተቀርጸው ተግባራዊ በመደረጋቸው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ስርዓት መዘርጋት ማስቻሉን ከፍተኛ አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ተነሳሽነቶች በረሃማ የነበረው የሶማሌና አፋር መሬት አንዱ የምርታማነት ማሳያ ተደርጓል፡፡ለአብነትም የአፋር ክልል የግብርና ስራን ብንመለከት በተለያዩ የምርት አይነቶች ምርትና ምርታማትን ማሳደግ ተችሏል እንደ ክልሉ መረጃ፡፡

በመላ ሀገሪቱ በግብርናው ዘርፍ ያሉ ማነቆዎችን በመፍታት የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚያሳድጉ ግብዓቶችን በማቅረብ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የሀገሪቱ ትልም ሆኖ ይህንኑ ለማሳካትም ርብርብ መደረጉ ተመላክቷል፡፡

ከለውጥ አመታቱ ወዲህ ትኩረት ያገኘው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ጨምሮ በአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ሰፋፊ ስራዎች መሰራታቸውን አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡

በዚህም ከውጭ ይገባ የነበረውን ስንዴን በሀገር ውስጥ ከመተካት አልፎ ወደ ውጭ በመላክ በመጀመሪያው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ቃል የተገባውን በተግባር ማረጋገጥ ተችሏል እንደ ፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ፡፡

በዚሁ የለውጥ አመታት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ብቻ ሳይሆን ውስን ቦታዎች ሳይቀሩ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ሁሉም ከጓሮው የምግብ ፍጆታውን እንዲሸፍን ጥረት ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

ይህም የኑሮ ውድነት ሊያስከትለው የሚችለውን ጫና በመቋቋም የሌማት ትሩፋት ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

ይሄው ጥረት የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ከተረጂነት የመላቀቅ እሳቤን ያረጋገጠ ለመጪው ትውልድም የሚተርፍ ስራ የተሰራበት መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮቹ የተናገሩት፡፡

የሀገሪቱ የግብርናው ዘርፍ ለውጥ በአመት አንዴ የማምረት ልምድን ወደ ሶስት ያሸጋገረ እና ግብርናው በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ምቹ እድል የፈጠረም ሆኗል፡፡

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review