ኢትዮጵያ አፍሪካዊ የልማት እቅድና ፕሮጀክቶች በአፍሪካዊ መለኪያና መስፈርቶች ብቻ እንዲመዘኑ በትብብር እንደምትሰራ ተገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ አፍሪካዊ የልማት እቅድና ፕሮጀክቶች በአፍሪካዊ መለኪያና መስፈርቶች ብቻ እንዲመዘኑ በትብብር እንደምትሰራ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 9/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ አፍሪካዊ የልማት እቅድና ፕሮጀክቶች በአፍሪካዊ መለኪያና መስፈርቶች ብቻ እንዲመዘኑ በትብብር እንደምትሰራ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የአፍሪካ መንግስታት እና ተቋማት መረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ መስጠት እንዲችሉ የሚረዳ የግምገማ ስርአት ለመዘርጋት የሚሰራው የአፍሪካ የግምገማ ማህበር (AfrEA) 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓሉን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው።

በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ መካሄድ በጀመረው የድርጅት ጥናታዊ ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሀገራት ፖሊሲ አውጪዎች፣ የግምገማ በለሙያዎች ፣ ተመራማሪዎች እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

አፍሪካን መሠረት ያደረጉ የአሰራር ዘዴዎችና የግምገማ ስርዓቶች ዕውቅና እንዲኖራቸው ማድረግ፣ ዓለም አቀፋዊ የግምገማ ስኬቶችን መቅረጽና አፍሪካዊ ተቋማት መረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ የመስጠት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ማስቻል በጥናታዊ ኮንፍረንሱ የተዳሰሱ ጉዳዮች ናቸው።

በመርሐ-ግብሩም ኢትዮጵያ አፍሪካዊ የልማት እቅድና ፕሮጀክቶች በአፍሪካዊ መለኪያና መስፈርቶች ብቻ እንዲመዘኑ በትብብር እንደምትሰራ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በድርጅቱ የብር ኢዮቤልዩ በዓል ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ እንግዶች የአዲስ አበባን አዳዲስ ገፅታዎች ይጎበኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review