ኢትዮጵያ እና ሞሪሺየስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ሞሪሺየስ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

AMN-የካቲት 9/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ከሞሪሺየስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቪን ራምጉላም ጋር ተወያይተዋል።

የሞሪሺየስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በፖለቲካ፣ በማኀበራዊ ፣ በባህል እና በኢኮኖሚ መስኮች ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬትንም አድንቀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው ፣ ኢትዮጵያ ከሞሪሺየስ ጋር በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በአቪዬሽን እና ሌሎች ዘርፎች ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አንስተዋል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ተጨማሪ የትብብር ዘርፎችን በማስፋት በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ ፖርት ሊዊስ ቀጥታ በረራ እንዲጀመር በማመቻቸት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት እንዳለው አስታውቀዋል፡፡

ውይይቱ ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን መካሄዱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review