ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባህል፣ በኪነ ጥበብ እና ስፖርት ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባህል፣ በኪነ ጥበብ እና ስፖርት ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

AMN- ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት የባህል፣ የኪነ ጥበብ እና ስፖርት ዘርፍ ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረጉ ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ ካላት የብዝሃ ባህል ባለቤት እና ታሪክ አንጻር ከሩሲያ ጋር በዘርፎቹ በጋራ መስራቷ ያለው አስፈላጊነት በውይይቱ ተነስቷል።

ኢትዮጵያ ለብሪክስ አባል ሀገራት ባህል እና የኪነ ጥበብ ሀብቷን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር እያከናወነች ያለውን ስራ የሩሲያ መንግስት በመደገፍ በትብብር እንደሚሰራም ተገልጿል።

ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸውን ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review