AMN-መጋቢት 12/2017 ዓ.ም
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በኬንያ የባርባዶስ ከፍተኛ ኮሚሽነር እና በናይሮቢ የተባበሩት መንግሥታት ቋሚ ተወካይ ከሆኑት ዊሊያም አሌክሳንደር ማክዶናልድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ውይይቱ የሰው ኃይል ልማት እና ስምሪት ዝርዝር አፈፃፀም ላይ ያተኮረ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ፣ ወደ ተግባር የሚሸጋገርበትን ውጤታማ ምክክር ማድረጋቸውን አመላክተዋል፡፡
ዊሊያም አሌክሳንደር ማክዶናልድ በትብብር ለመሥራት ላሳዩት ቁርጠኝነትም አመሥግነዋል፡፡