ኢትዮጵያ እና ቱርክሜኒስታን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና ቱርክሜኒስታን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያዩ

AMN – መጋቢት 30/2017

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከቱርክሜኒስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራሺድ መርዶቭ ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በስልክ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው፣ የሁለቱን ሀገራት ትብብር በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ለማሳደግ እንዲሁም የሀገራቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ማጎልበት፣ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር መተባበርን እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለመፍጠር በጋራ መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

እንዲሁም ዘርፈ ብዙ እና ዘላቂ ግንኙነትን ለመገንባት ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለጹት ሚኒስትሮቹ፣ የከፍተኛ ባለስልጣናት ጉብኝት እንዲደረግ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያ እና ቱርክሜኒስታን በቀጣይ በምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት ዘርፍ ባሉ ዕድሎች፣ በቀጣናዊ መረጋጋት እና ትብብር ላይ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው አንስተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review