ኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ይሰራል- ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

AMN – ህዳር 3/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼይ ሀይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይለወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት ላይ መድረሱን በማስታወስ፤ ይህን ጠንካራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ዶketር ጌዲዮን የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በአፍሪካ ቻይና የትብብር መድረክ (ፎካክ) ማዕቀፍ ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ለመተግበር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያም ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን በባለብዙ ወገን ግንኙነት በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ እንደምትሰራ ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼይ ሀይ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተላከውን የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አምባሳደሩ በፎካክ ጉባዔ ላይ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች መግባባት ላይ የደረሱባቸውን የኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review