ኢትዮጵያ እና አርሜንያ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለፁ

You are currently viewing ኢትዮጵያ እና አርሜንያ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለፁ

AMN- ሰኔ 3/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እና አርሜንያ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን በተለያዩ የትብብር መስኮች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገልፀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የአርሜንያ ሪፐብሊክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫሃን ኮስታኒያን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአርሜንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ቫሃግን ካቻቱሪያን የተላከ መልዕክት ለፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ አቅርበዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ ኢትዮጵያ እና አርሜንያ ጥልቅ እና ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው በማንሳት፥ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም እያደረገች ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ የአርሜንያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ በባህል እና በትምህርት ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቫሃን ኮስታኒያን በበኩላቸው አርሜንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review