ኢትዮጵያ እና ኪርጊስታን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።
በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በጣሊያን የኪርጊስታን አምባሳደር ታላይ ባዛርቤይቭ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፣ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸውን መደጋገፍ የበለጠ ለማጠናከር ከመግባባት ላይ ደርሰዋል።
አምባሳደር ደሚቱ፣ ኪርጊስታን ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፈት ለያዘችው እቅድም ሂደቱን ለማፋጠን አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ማረጋገጣቸውን በሮም ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።