AMN-የካቲት 28/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ረመዳን መሐመድ አብደላ ጎክ ጋር በጁባ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው፣ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳንን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እና ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ከስምምነት ደርሰዋል።
የሀገራቱን የኢኮኖሚ ትብብር እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩም መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።