
AMN-ኅዳር 18/2017 ዓ.ም
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ብሌድ ንዚማንዴ (ዶ/ር) ጋር በሁለቱ ሀገራት የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካካል በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እ.አ.አ ሰፕቴምበር 10/2021 በጋራ ለመስራት በተፈረመው ስምምነት መሰራት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ለመጎብኘት፣ ለመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ውጤታማነት የአስር አመት ሀገራዊ እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ በሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲሁም ዲጂታላይዜሽን ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካላት ደቡብ አፍሪካ የምርምርና ልማ፣ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኮመርሻላይዘሽን፣ኢኖቬሽንና ኢንዱስትሪያላይዜሽን፣የሰው ሀብት ልማት፣የምርምር ባለሙያዎች ትብበር እንዲሁ የጋራ መሰረተ ልማት ዝርጋታና አጠቃቀም ዙርያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማነት የአፍሪካዊያንን ትብብር ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሼን ሚኒስትር ብሌድ ንዚማንዴ (ዶ/ር) ደቡብ አፍሪካ በስፔስና አስትሮኖሚ፣ በምርምርና ኮመርሻላይዜሽን፣በባዮ ኢኮኖሚ፣በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣በናኖቴክኖሎጂ እና የሰው ሀይል ልማት ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማከፈል እና የኢትዮጵያን ልምድም ለመቅስም ዝግጁ መሆንን ተናገግረዋል፡፡
በቀጣይ በናኖ ቴክኖሎጂ፣በስፔስ ሳይንስና አስትኖሚ በማቴሪያል ሳይንስ እንዲሁም በሰው ሀብት ልማት ትኩረት በመስጠት የአፍሪካን የ2063 አጀንዳ አፍሪካዊያንን በማስተባበር እንዲሁም ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት በመስጠት መሰራት እንደሚገባ አንስተዋል።

በአሀጉሩ የተበታተነውን የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ስራን በተቀናጀ መልኩ መምራት ለአሀጉሩ የዘርፉ ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑን የስራ ኃላፊዎቹ በማንሳት ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ያላቸውን ትብብር በማጠናከር ሌሎችን የአፍሪካ ሀገራት መሳብና ማቀናጀት እንደሚጠበቅባቸው ተግባብተዋል።
በስምምነቱ በስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአስትሮኖሚ ሁለት ፕሮጀክቶች በባዮና ኢመርጅንግ ቴክኖሎጂ አምስት ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ሰባት ፕሮጀክቶች በሁለቱ ሀገራት ትብብር እየተሰሩ ይገኛሉ።
ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ በባዮና ኢመርዲንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ አየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የተጎበኙ ሲሆን ስራዎቹ አመርቂ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆኑ ተጠቅሶ ሊሰፉ እንደሚገባ ተነስቷል።
በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ የጋራ ሰራዎችን ለመስራት የሚየስችል የጋራ ፈንድ በማፈላለግና በመመደብ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!