ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር ያለመ ምክክር እየተካሄደ ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያላትን ትብብር ማጠናከር ያለመ ምክክር እየተካሄደ ነው

AMN- የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፖሊሲ ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም አምባሳደር ዳረን ዌልች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ምክክሩ እየተካሄደ የሚገኘው “በኢትዮጵያ እና አጋሮቿ መካከል ዘላቂ አጋርነት መገንባት ለስትራቴጂካዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

ውይይቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ትብብር በማጠናከር የጋራ እድገት እና ትብብርን እውን ማድረግ መሆኑ ተመላክቷል።

በፖሊሲ ምክክሩ የተለያዩ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይየት ይደረግባቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review