AMN – ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የ2025 የብሪክስ ፕሬዚደንትነት ለተረከበችው ብራዚል የእንኳን ደስ አለሽ መልእክት አስተላልፋለች፡፡
ኢትዮጵያ ብራዚል በብሪክስ ፕሬዚደንትነት ጊዜያዋ ፍትሃዊ፣ አካታች እና ውጤታማ የአለምአቀፍ አስተዳደርን ለማስቀጠል የሰነቀችውን ራዕይ እንደምትደግፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለመፍጠር እና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላትም ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡