ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከእስራኤል ጋር ትብብሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከእስራኤል ጋር ትብብሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ

AMN – ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በዘርፉ የተሻለ ልምድ ካላት እስራኤል ጋር ትብብሯን አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጤሞቴዊስ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ፣ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ከፍተኛ የንግድ ልዑካን ቡድን መርተው አዲስ አበባ ከገቡት የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ጋር ተወያይተዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት በሁለንተናዊ ዘርፎች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጤና፣ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ እና መሰል ዘርፎች በተሻለ ትብብር ለመስራት ሁለቱ ሚኒስትሮች መወያየታቸውም ተመላክቷል፡፡

ጌዲዮን (ዶ/ር) አክለውም ሽብርተኝነት የጋራ ጥላት በመሆኑ ከእስራኤል ጋር ትብብራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋና መግቢያ በር በመሆኗ የእስራኤል ሁነኛ አጋር ነች ብለዋል።

ሚኒስትሩ፣ በዚህ ሥልጣናቸው በኢትዮጵያ ዛሬ የጀመሩት ጉብኝት በአፍሪካ የመጀመሪያው መሆኑን ገልጸው፣ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ታሪካዊ እና ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በኢኮኖሚ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እስራኤል ቁርጠኛ መሆኗን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review