ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አቅም ለመጠቀም በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ላይ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አቅም ለመጠቀም በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ላይ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

AMN-ሰኔ 3/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ አቅሞች ከተቀረው ዓለም ጋር በጥብቅ ለማስተሳሳር ያለመ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ውይይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የተለያዩ ባለድርሻ ተቋማት ተወካዮች እየተሳተፉበትም ይገኛል።

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም በአለም አቀፍ ደረጃ ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል፡፡

በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን ምቹ የፖሊሲ ከባቢ በማስተዋወቅ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ፣ ሀገሪቷ ያላትን የገበያ አቅም ለማሳየት እና የንግድ ግንኙነትን ለማጎልበት እንደ መሸጋገሪያ ድልድይ እያገለገለ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ዕድሉን በሚገባ በመጠቀም ኤምባሲዎች እና ሚሲዮኖች የውጭ ኢንቬስተሮችን ለመሳብ እንዲጠቀሙበት እና ይበልጥ እንዲሰሩም ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ምዕራፍ ውስጥ እየገባች ባለችበት በአሁኑ ጊዜ፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ከፍ ያለ ስትራተጂያዊ ጠቀሜታ እንዳለው የተመላከተ ሲሆን በተለይም የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እቅሞች ከዉጪዉ አለም ጋር በጥብቅ ለማስተሳሰር የበለጠ ትኩረት ያሻዋል ተብሏል።

በአሰግድ ኪዳነማሪያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review