ኢትዮጵያ 46ኛው የካፍ መደበኛ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን በሚገባ ተዘጋጅታለች፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ኢትዮጵያ 46ኛው የካፍ መደበኛ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን በሚገባ ተዘጋጅታለች፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ኢትዮጵያ 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን በሚገባ ተዘጋጅታለች ብለዋል ፡፡

ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያ እያስተናገደች ከምትገኘው 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጉባኤ አስቀድሞ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔን እና የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከፍተኛ አመራሮችን በጽሕፈት ቤታቸው መቀበላቸውንም አመልክተዋል።

በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የአደይ አበባ ስታዲየምንም መጎብኘታቸውንና ኢትዮጵያ ይህ ጠቃሚ ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን ለማገዝ በሚገባ ተዘጋጅታለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review