ኢትዮጵያ 6ኛውን የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ሴት ነጋዴዎች የንግድ ኤግዚቢሽን ልታካሂድ ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ 6ኛውን የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ሴት ነጋዴዎች የንግድ ኤግዚቢሽን ልታካሂድ ነው

AMN – የካቲት 26/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ 6ኛውን የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ሴት ነጋዴዎች /COMFWB/ የንግድ ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንስ ልታካሂድ ነው፡፡

የንግድ ትስስር እና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ያስሚን ወሀብረቢ የንግድ ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንሱን አስመልከቶ ከ COMESA ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ማውሪን ሱምብዌ ጋር በቢሯቸው ተወያይተዋል፡፡

የንግድ ኤግዜቢሽን እና ኮንፈረንሱ ለኢትዮጵያ እና ለ COMESA አባል ሀገራት ነጋዴ ሴቶች የገበያያ ትስስር፣ ንግድን ለማስፋፋት እና የፋይናንስ አቅማቸውን ለማጠናከር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ሚኒስትር ዴኤታዋ በውይይታቸው አንስተዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነጋዴ ሴቶችን ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ነዳዴ ሴቶች ማህበርን በአዲስ መልክ ማስመረጡን ገልፀው ይህን የንግድ ኤግዚቢሽንም የአፍሪካ መዲና በሆነቸው አዲስ አበባ መካሄዱ ትክክለኛ ጊዜ ነው ብለዋል፡፡

የኮሜሳ ነጋዴ ሴቶች ፌዴሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ማውሪን ሱምብዌ በበኩላቸው፣ ይህንን የንግድ ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንስ ለማካሄድ ኢትዮጵያ ምቹ እንደሆነች ገልጸዋል፡፡

የንግድ ኤግዚቢሽን እና ኮንፈረንሱ በተለይም ለኢትዮጵያ ሴት ነጋዴዎች በጣም ጠቃሚ መሆኑን ማንሳታቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review