ኢትዮ ቴሌኮም “ዘመን ገበያ” የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ገበያ አስጀመረ

You are currently viewing ኢትዮ ቴሌኮም “ዘመን ገበያ” የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ገበያ አስጀመረ

AMN – ሚያዝያ 30/2017

ኢትዮ ቴሌኮም “ዘመን ገበያ” የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ገበያ ማስጀመሩን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም “ዘመን ገበያ” የተሰኘው ቴክኖሎጂ፣ የኢትዮጵያን የንግድ ስርዓት በቴክኖሎጂ ለማስተሳሰር የተሰራ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልፀዋል።

“ዘመን ገበያ” ዲጂታል መገበያያ ገበሬውን ከገዥ ጋር፣ ነጋዴውን ከአምራቹ ጋርና ሌሎችንም ዘርፎች እንደሀገር የሚያገናኝ መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አንስተዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም፣ ቴክኖሎጂው የኑሮ ውድነትን የሚያባብሱ ህገ ወጥ ደላላዎችን ከስርዓቱ ውጭ በማድረግ ሁሉም የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በኢትዮ ቴሌኮም ታሪክ ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ሂደት ሀገር አቀፍ ዲጅታል ግብይት መፍጠር ላይ በር ከፋች ስለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡

“ዘመን ገበያ” ንግድን በማቀላጠፍ፤ የሥራ ዕድል በፍጠርና የኢኮኖሚ እድገት ላይ አካታችና ሰፊ የገበያ ተደራሽነት ያለው፣ ለአገር ውስጥ ምርትና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እድገትንና የሥራ ፈጠራን በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ተብሏል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review