ኢትዮ ቴሌኮም 5ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ አስጀመረ

You are currently viewing ኢትዮ ቴሌኮም 5ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በቢሾፍቱ ከተማ አስጀመረ

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም በቢሾፍቱ ከተማ የአምስተኛ ትውልድ (5ጂ) የኢንተርኔት አገልግሎትን አስጀምሯል።

በዚህ ዓመት 15 ከተሞችን የ5ጂ ኔትዎርክ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ የያዘው ተቋሙ፤ ቢሾፍቱን የዚህ ፈጣን የኔትዎርክ አገልግሎት ተጠቃሚ አድርጓል።

የቱሪስት መዳረሻ የሆነችው ቢሾፍቱ ከተማ የ5ጂ ኔትዎርክ ሽፋን ማግኘቷ ያላትን ዕምቅ አቅም የበለጠ እንድትጠቀም የሚረዳ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዋንም የሚያሳድግ ነው ተብሏል።

አገልግሎቱን ያስጀመሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተቋማቸው የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከዘርፉ ጋር እኩል እንድትጓዝም የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በአሰግድ ኪዳነ ማሪያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review