ኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ተከፈተ

You are currently viewing ኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ተከፈተ

AMN – መጋቢት 4/2017 ዓ.ም

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ የኤግዚቢሽን ማዕከል የተዘጋጀውን የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከፍተዋል።

በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ፣ የሀገራት አምባሳደሮች፣ የምርት እና አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት የሀገር ውስጥን ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ዓለም ሀገራት የመጡ አምራች ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።

ዓለም አቀፉ የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያን ምርትና አገልግሎቶች በማስተዋወቅ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የገበያ ትስስር እና የልምድ ልውጥጥ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

በዚህም በሀገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች እና ከውጭ ሀገራት በመጡ የንግድ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶች ቀርበው የአቻ ለአቻ የንግድ የምክክር መድረክ እንደሚካሄድ መገለፁንም ኢዜአ ነው የዘገበው።

“የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው 14ኛው የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆም ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review