ኢንዱስትሪዎች በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን በቴክኖሎጂ መታገዝ እንዳለባቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ

You are currently viewing ኢንዱስትሪዎች በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን በቴክኖሎጂ መታገዝ እንዳለባቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ

AMN- ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም

ኢንዱስትሪዎች በገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመታገዝ መስራት እንዳለባቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል።

በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አካል የሆነ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ-ግብሩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ ኢንደስትሪዎች በቴክኖሎጂ ተደግፈው መስራት እንደሚኖርባቸው ጠቁመው ይህ ካልሆነ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ ለመሆን አዳጋች መሆኑን ገልጸዋል።

ሎጂስቲክስ እና አገልግሎት አሰጣጥ ሳይሻሻል የኢንዱስትሪ ዘርፉ ሊያድግ እንደማይችልም ነው የተናገሩት።

የፓናል ውይይት መድረኩ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያሚያተኩር መሆኑ ተመላክቷል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review