ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ በህዝብና በመንግስት መካከል ድልድይ ሆኖ መቀጠል እንደሚገባው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ በህዝብና በመንግስት መካከል ድልድይ ሆኖ መቀጠል እንደሚገባው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

AMN- ግንቦት 28/2017 ዓ. ም

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ በህዝብና በመንግስት መካከል ድልድይ ሆኖ መቀጠል እንደሚገባው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

የራዲዮ ጣቢያው የተሰሩ ስራዎች እና የተፈቱ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን በአግባቡ ማድረሱን መቀጠል እንዳለበትም ከንቲባዋ ለኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 ገልጸዋል።

ኤፍ ኤም 96.3 በቀጣይም ትክክለኛው የህዝብ ድምፅ በማስተጋባት ለከተማዋ ነዋሪዎች ታማኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን መስራት እንደሚገባውም አሳስበዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀጣይ ኤፍ ኤም 96.3 የጀመራቸውን ስራዎች እንዲያጠናክር የከተማ አስተዳድሩ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልፀዋል።

በወንድምአገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review