እስራኤል በኢራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ ሆሴይን ሳላሚ መገደላቸው ተሰማ

You are currently viewing እስራኤል በኢራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ ሆሴይን ሳላሚ መገደላቸው ተሰማ

AMN – ሰኔ 06/2017 ዓ.ም

እስራኤል የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ማዕከል ላይ ያነጣጠረ ነው ባለችው ጥቃት የአገሪቱ ጦር ኃይሎች አንደኛው ቅርንጫፍ የሆነው የኢራን አብዮታዊ ዘብ ዋና አዛዥ ሆሴይን ሳላሚ ተገድለዋል።

ከሆሴይን ሳላሚ በተጨማሪም ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት እንዲሁም ስድስት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መገደላቸውን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል።

ኢራን በምላሹ 100 ያህል ድሮኖችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፏን እና አብዛኛዎቹ መክሸፋቸውን የእስራኤል ጦር ሃይል አስታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟ ጉዳይ በፍጥነት ወደ ስምምነት ካልመጣች ሌሎች አስከፊ ጥቃቶች በእስራኤል ሊፈፀሙባት እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ሆሴይን የአብዮታዊ ዘብን የተቀላቀሉት የኢራን ኢራቅ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ እ.ኤ.አ በ1980 ነበር።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review