ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተዉጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በጅማ ዞን ጉብኝት እያካሄዱ መሆናቸዉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልአዚዝ ራያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደተናገሩት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎቹ በጅማ ከተማና በጅማ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘ ላይ ይገኛሉ፡፡
ባለሙያዎቹ በማና ወረዳ ሞዴል የገጠር ኮሪደር ልማት ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ስራዎችን በመመልከት ላይ ይገኛሉ፡፡
የቡና ልማት ፤ ንብ ማነብ፤ የሻይና ሙዝ ልማት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከጎበኟቸዉ የልማት ስራዎች መካከል ሌሎቹ ናቸዉ፡፡
ከሁለት መቶ የሚበልጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት በዞኑ የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልአዚዝ ራያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስርን ጨምሮ ሌሎች የጅማ ዞንና ከተማ አመራሮች በዞኑና በከተማዉ የተሰሩና በመሰራት ላይ ያሉ በርካታ የልማት ስራዎችን በማስጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ