AMN-ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
በተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ)፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በአፍሪካ ኅብረት አዘጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄድ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በኮንፈረንሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት እና የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ተገኝተዋል።