ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽ ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-
በተለያዩ ዘርፎች ሲከናወኑ የነበሩ ሪፎርሞችን አጠናቀን ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዘመን የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ተገኝተናል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ተመዝግቧል፣ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ስኬት ነው፡፡
በዘንድሮው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል፡፡
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት ከፍተኛ ስራ ተከናውኗል፡፡
የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 67 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡
የኢንዱስትሪ ዘርፉ በተያዘው በጀት ዓመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡
የሌማት ትሩፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ እድገት የተመዘገበበት ዘርፍ ሆኗል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት ምርቶች የ5 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ያስመዘግባሉ