
AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ340 የፓሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤት ማስተላለፋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታወቁ ፡፡
2ኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ለመተግበር የፖሊሶችን ካምፕ ስንጎበኝ የሰራዊቱ አባላት ካምፕ ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው እና ከልጆቻቸው ጋር እጅግ በማይመች ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ መሆኑን በመረዳት ለነዋሪዎች እንዳደረግነዉ ሁሉ ለ340 ቤተሰብ ላላቸው የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤቶችን አስተላልፈናል ብለዋል ።

ፖሊስ ቅድሚያ ለህዝብ በማለት ለሀገር ደህንነት ዋጋ እየከፈለ የሚገለግል እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ለሰራዊቱ ምቹ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖረዉ ከተቋሞቻቸዉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምንሰራ ይሆናል ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው::
