ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማህበረሰቡ የስፖርትን ጥቅም ተረድቶ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ

AMN – ታኅሣሥ -5/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ጠንካራ የስፖርት ምክር ቤት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ 15ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂደናል ብለዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የከተማችንን የስፖርት እድገት ለማረጋገጥ እንዲሁም በአካል እና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለመገንባት በርካታ ስራዎች የሰራን ሲሆን፣ በከተማችን 1,314 የህፃናት እና ወጣቶች የመጫዎቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ገንብተን ለአገልግሎት አብቅተናልም ብለዋል።

ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት በ11ዱም ክፍለ ከተሞቻችን 128 የታዳጊ ወጣቶች የስፖርት ስልጠና መርሃ-ግብሮችን ከፍተን በመስራት ላይ እንገኛለንም ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡም የስፖርትን ጥቅም ተረድቶ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተሳትፎ እንዲያደርግ ከንቲባዋ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review