ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጀርመን አደባባይ አካባቢ በመገንባት ላይ የሚገኙት የመኖሪያ ቤቶች የደረሱበትን ደረጃ መገምገማቸውን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጀርመን አደባባይ አካባቢ በመገንባት ላይ የሚገኙት የመኖሪያ ቤቶች የደረሱበትን ደረጃ መገምገማቸውን ገለጹ

AMN – ሰኔ 06/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጀርመን አደባባይ አካባቢ በመንግስት በጀት በመገንባት ላይ የሚገኙት የመኖሪያ ቤቶች የደረሱበትን ደረጃ ገምግመናል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ከተጀመረ 9 ወር የሆነዉ ይህ ግንባታ በጥራት እና በፍጥነት ወደ ማጠናቀቂያዉ ላይ በመሆኑ ቀሪ ስራዎችን በመጨረስ ተጨማሪ የቤት አቅርቦት የመጨመር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በአሁኑ ሰአት ያለዉ የቤት ፍላጐት በመንግስት ብቻ ሊመለስ የሚችል ባለመሆኑ በቤት ግንባታ ስራ ላይ የተሰማራችሁ የግል አልሚዎችም የቤት አቅርቦትን መጨመር የከተማችን ትልቁ ትኩረት መሆኑን በመገንዘብ እና መንግስት እንዲህ በአጭር ጊዜ መገንባት ከቻለ ከግሉ ዘርፍ ከዚህ በላይ ስለሚጠበቅ የጀመራቹሃቸውን ግንባታዎች በፍጥነት እና በጥራት እድታጠናቅቁ ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም መሬት አጥራችሁ ግንባታ ያልጀመራችሁም በፍጥነት ጀምራችሁ በማጠናቀቅ ለቤት ፈላጊዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አብራችሁን እድንትሰሩ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊዉን ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review