AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠናዊ ምክትል ፕሬዝዳንት ከሆኑት ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር) ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ውይይታቸውን አስመልክተው ከንቲባ አዳነች በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በሰው ተኮር ስራ፣ በምገባ መርሃ ግብር፣ በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ፈጣን ለዉጦች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
በከተማ ንፅህና አጠባበቅ እና ፍሳሽ አወጋገድ እንዲሁም የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የጀመርነው ዘመናዊ የትራፊክ ስርዓት ዝርጋታ ስራ የሚበረታታ በመሆኑ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸውልናል ነው ያሉት።