AMN – ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ሚስተር ሹ ኩንሊን በህዳር ወር በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የጂያንግሱ ግዛትን እንድንጎበኝ ባቀረቡልን ግብዣ መሰረት በግዛቱ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
በጉብኝታችን ወቅት ከጂያንግሱ ግዛት አስተዳዳሪ እና አመራሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በመወያየት በቀጣይ በጥቅሉ በኢንቨስትመንት ፣ በንግድ ፣ በቱሪዝም ፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፎች ላይ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በቀጣይም በትብብር ለመስራት ተግባብተናል ሲሉ አመልክተዋል።
ሚስተር ሹ ኩንሊን በጂያንግሱ ግዛት በነበረን ጉብኝት ላደረጉልን መስተንግዶ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል።