ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት “ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል!” በሚል መሪ ቃል በየደረጃው ሲካሄድ የነበረው የመምህራን ውይይት የማጠቃለያ መድረክ አድርገናል ብለዋል።
መድረኩ ለሀገር ግንባታ መምህራን ያላቸውን ታላቅ ሚና በመረዳት በሀገራዊ ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ እንዲሁም ከመምህራን የሚነሱ ጥያቄዎችን እና ሃሳቦችን በማዳመጥ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው::
መምህራንና ቤተሰቦቻቸው በነፃ የሚታከሙበት ሆስፒታል ግንባታን ጨምሮ ሌሎች መምህራኑ ያነሷቸውን ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ በዘላቂነት ለመፍታት ተግባብተናል ሲሉም ነው ከንቲባ አዳነች የገለፁት።
መምህራኖች የትውልድ ግንባታ ስራችንን በመገንዘብ እዉቅና የሰጡ ሲሆን እኛም ላበረከቱት አስተዋፆኦ ሁሉ ከልብ አመስግነናለንም ብለዋል ከንቲባ አዳነች።