ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለተመረቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለተመረቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

AMN- ሰኔ 15/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከአንጋፋው ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተመረቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ውድ ተመራቂዎች፤ የትምህርት ዘርፍ ተመራቂ እንደመሆናችሁ መጠን ትምህርት ትውልድን የሚቀርጽና የሚያንጽ መሳሪያ መሆኑን፣ መማር ደግሞ የአስተሳሰብ እና የአሰራር ለውጥ ማምጣት የሚስችል እንዲሁም የትምህርት ባለሞያነት ትውልድን በማነጽ ሃገርን የመገንባት የማይተካ ታላቅ ሃላፊነት ስለሆነ ስራ ላይ ስትሰማሩ ለአፍታም ሳትዘናጉ ለዉጤታማነቱ ልትተጉ ይገባል ብለዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቻችን ወጣቶች ናቸሁ፣ መጪው ጊዜ ደግሞ የወጣቶች ነው፤ ከዛሬው የተሻለ ብሩህ ተስፋ ይጠብቃችኋል በማለትም አክለዋል።

ለሚጠብቃችሁ ብሩህ ዘመን የተማራችሁትን ወደ ተግባር መለወጥ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ተማሩ፤ እየተለወጠ ላለዉ ነገ ራሳችሁን ይበልጥ አዘጋጁ ሲሉም ነው አደራ ያስተላለፉት።

የስራ ዘመናቸውም ስኬታማ እንዲሆን ልባዊ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review