ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

AMN-ሚያዚያ 11/2017 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!

የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከሃጢያት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል ነው።

እኛም እየሱስ ክርስቶስን በተምሳሌትነት በመከተል እርስ በርስ በመፋቀር፣ በመተሳሰብ፣ በይቅርታና ምህረት በማድረግ ከሰዉ ልጆች ጋር ሁሉ በሰላም እንድንኖር እሱ ይርዳን።

በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመተሳሰብ፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review