የትንሳኤ በዓልን የኮሪደር ልማት ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ፣ኮንትራክተሮች እንዲሁም አማካሪዎች ጋር በስራ ቦታ ማክበራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ሰራተኞቹ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ እና አዲስ ለማድረግ ቀን ከሌት ለሚያደርጉት ትጋት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል፡፡