ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባን እንደገና እየሰሯት ነው- ፋይናንሺያል ታይምስ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባን እንደገና እየሰሯት ነው- ፋይናንሺያል ታይምስ

AMN-የካቲት 29/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአፍሪካ መዲናን እንደገና እየሰሯት ነው ሲል ዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን ፋይናንሺያል ታይምስ በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል፡፡

ፋይናንሺያል ታይምስ ባወጣው ዘገባ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተቸገሩ ደራሽ፣ የድሆችን ቤት የገነቡ እና የኢትዮጵያን ዋና ከተማ እያስዋቡ ያሉ ሲል አሞካሽቷቸዋል፡፡

የከተማዋ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ የሆኑት አዳነች አቤቤ፣ የ6 ሚሊየን ህዝብ መኖሪያ እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባን በማዘመን በአህጉሪቱ ካሉ ዘመናዊ ከተሞች አንዷ እያደረጓት መሆኑን አመላክቷል፡፡

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ እና በአሁኑ ሰዓት በለንደን ሶአስ ፕሮፌሰር የሆኑት አርከበ እቁባይን ያነጋገረው ፋይናንሺያል ታይምስ፣ “ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ጀምሮ ንጉሠ ነገሥታቱ ለከተማዋ እድገት ዕቅድ ነበራቸው” ሲሉ ማብራራታቸውን ገልጿል፡፡

በፈረንጆቹ 1960ዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የአፍሪካ አዳራሽ እና የከተማውን አዳራሽ ጨምሮ ‘ይህችን ታላቅ መንደር’ ከተማ እንድትሆን እና እውነተኛ ታላቅ ዋና ከተማ ለማድረግ የአውሮፓ እና የእስራኤል አርክቴክቶችን ያመጡት ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ እንደነበሩም አመላክቷል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ረጃጅም ሕንፃዎች የተገነቡባት እና ለብዙሃን መኖሪያነት የተመቸች ብዙ መደላድል የሞላባት ከተማ ሆናለች ሲልም ዘገባው አክሏል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review